ሰሊሆም የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር የሚሰራቸው ስራዎች
በየጎዳና የወደቁ የአዕምሮ ህሙማን ወገኖቻችንን ከጎዳና በማንሳት መጀመሪያ ገላቸው በማጠብ ልብሳቸውን በመቀየር ህክምና ክትትል እንዲያደርጉ በማድረግ ምግባቸውን መኝታቸውን በማመቻቸት ተገቢውን ድጋፍ ፍቅር በመሰጠት ጤናቸውን ወሰተሻለ ደረጃ እንዲደርስ ማስቻል በክትትሉም ለውጥ ያመጡ የዳኑ ሰዎችን የተለያዩ ስልጠና እንዲያገኙ በማድረግ ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ማገዝ ህይወታቸው የተሻለ የተሳካ እንዲሆን እገዛ ድጋፍ ማድረግ፡፡ ጧሪ ቀባሪ የሌላቸው አዛውንቶችን የሀገር ባለውለታዎችን ከወደቁበት በማንሳት ቀሪ ዘመናቸውን በተረጋጋ ሁኔታ ያለ ስጋት ይኖሩ ዘንድ ህክምና ክትትላቸውን እያደረጉ እንክብካቤ ፍቅርን በመስጠት ቀሪ ዘመናቸውን በነጻነት እንዲኖሩ ማስቻል፡፡ የአዕምሮ ህመም የገጠማቸውን ቤተሰብ ተንከባካቢ የሌላቸውን ህጻናት በመቀበል እንክብካቤ ፍቅር በመስጠት የህክምና ክትትል እንዲያደርጉ በማድረግ የተሸለ የጤና ሁኔታ ላይ እንዲደርሱ ማስቻል፡፡
ህሙማኑን ለመርዳት፥
-ኑ! ማህበሩን ጎብኙልን
-ኑ! ለህሙማን ፍቅር እና እንክብካቤ እንስጣቸው
-ኑ! ልብሳቸውን እና ገላቸውን እንጠብ
-ኑ! ፍቅር በመስጠት ከገቡበት የጤና መጉደል እንታደጋቸው
-ኑ! ከህሙማን ጋር በመመገብ ለነሱ ያለንን ወገናዊ ፍቅር እንግለፅላቸው
የማህበሩ አካውንት
የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ:- 1000275107518
አቢሲንያ ባንክ:- 77984852
አዋሽ ባንክ:- 01303572131300
የማህበሩ መቋቋም ጠቀሜታዎች
- ህሙማን በተረጋጋ ቦታ እንዲቆዩ ይረዳል
- ህክምናውን በሰዓት እዲያገኙ ይረዳል
- ስልጠና የሚያገኙበትን ሁኔታ ምቹ ያረገዋል...
የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶች
ማህበሩ የራሱ የሆነ ቋሚ ቦታም የለውም በኪራይቤት ነው ያለው ማህበሩ የራሱ መተዳደሪያ የለውም የሚተዳደረውም የማህበሩ በጎ ፈቃደኞች ጫማዎችን በመጥረግ መኪና በማጠብ በተለያዩ ክብረ በአላት ቆዳ በማሰባሰብ ገቢ ለማግኘት እየሰራ ያለ ማህበር ነው በተጨማሪም ወደ ማእከሉ የሚመጡ በጎ ፈቃደኞች በሚያደርጉት የገንዘብ የማቴርያል ድጋፍ እየተንቀሳቀሰ ያለ ማህበር ነው፡፡
ማህበሩን በማቴርያል ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ
- በምግብ ግብአት አቅርቦት
- በህክምና ቁሳቁሶች እና መድሀኒቶች አቅርቦት
- በንጽህና መጠበቂያ አቅርቦት
- በተለያዩ አልባሳት
በተጨማሪም ማህበሩን
- በእውቀታችሁ
- በጉልበታችሁ
- በሙያችሁ ድጋፍ ብታደርጉልን::
በማህበሩ ያሉ የአባላት ቁጥር እና የአዕምሮ ህሙማን በፐርሰንት
በማህበሩ ያሉ የአጋር እና የክብር አባላት ቁጥር
1. በማህበሩ ያሉ አባላት ቁጥር 50
2. በማህበሩ ያሉ የክብር አባላት ቁጥር 25
ማእከሉ ያሉ ወጣት የአዕምሮ ህሙማን በፐርሰንት 80%
1. በማእከሉ ካሉ ወጣት የአዕምሮ ህሙማን ወንዶች 50%
2. በማእከሉ ካሉ ወጣት የአዕምሮ ህሙማን ወንዶች 30%
በማእከሉ ውስጥ ያሉ አዛውንቶች በፐርሰንት 20%
1. በማእከሉ ያሉ ወንድ አዛውንቶች በፐርሰንት 9%
2. በማእከሉ ያሉ ሴት አዛውንቶች በፐርሰንት 11 %
በማእከሉ ውስጥ ያሉ የአዕምሮ ህመም ያለባቸው ህጻናት በፐርሰንት 7%
1. በማእከሉ ውስጥ ያሉ የአዕምሮ ህመም ያለባቸው ወንድ ህጻናት በፐርሰንት 3 %
2. በማእከሉ ውስጥ ያሉ የአዕምሮ ህመም ያለባቸው ሴት ህጻናት በፐርሰንት 4 %
ሊሰራ የታሰበው ህንፃ ዴዛይን